ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አንድን ግለሰብ ዒላማ አድርጎ በመመልመል፣ ነፃነቱን በመገደብ እና በመበዝበዝ የሚፈፀም ነው።
የብዝበዛ ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- ወሲባዊ ብዝበዛ ለምሳሌ፣ አስገዳጅ ዝሙት አዳሪነት
- የጉልበት ብዝበዛ እና ኢሰብአዊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ለመስራት ማስገደድ፣ ለምሳሌ በቤት ውስጥ፣ በእንክብካቤ፣ በግብርና፣ በግንባታ ወይም በእንግዳ ተቀባይነት ኢንዱስትሪዎች ውስጥ
- እንደ ስርቆት፣ ልመና ወይም የአካል ክፍሎች ልገሳ የመሳሰሉ የወንጀል ድርጊቶችን ወይም ሌሎች ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ ማስገደድ
ሴቶች፣ ወንዶች፣ ጎልማሶች እና ህጻናት የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ/ተጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ።
አብዛኞቹ በችግሩ የሚጠቁ ሰዎች ከሌላ አገር ነው የሚመጡት።
በሐሰት ተስፋ ተታለው ወደ ስዊዘርላንድ እንዲመጡ ይደረጋሉ።
"አፍቃሪ ወንዶች" ተብለው የሚታወቁት ደግሞ ወጣት ሴቶችን እንደሚወዱ እና እንደሚንከባከቡ አስመስለው ያታልላሉ።
ከዚያም በተደራጀ መልኩ ወጣት ሴቶችን ጥገኞች ያደርጓቸዋል፣ ብቸኛ ያደርጓቸዋል እና ወሲባዊ ወይም የወንጀል ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ ያስገድዷቸዋል።
አንድ ተጎጂ ሰው በስዊዘርላንድ በሕጋዊ መንገድም ይሁን በሕገወጥ መንገድ ቢኖር ምክር እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው።